KMN -Kalacha Media Network

KMN -Kalacha Media Network voice of justice & equality! provides news & informations
የፍትህና የእኩልነት ድምፅ! KMN - በመረጃ ጥራት ለማህበረሰብ የመረጃ ምንጭ እንሆናለን!

አንዲት እናት በአንድ ጊዜ አምስት ልጆችን በሰላም ተገላገለች!በትግራይ ክልል አበርገለ የጭላ ወረዳ በሚገኘው የጭላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከስምረት ጤና ጣቢያ የመጣች አንዲት እናት አምስ...
08/09/2026

አንዲት እናት በአንድ ጊዜ አምስት ልጆችን በሰላም ተገላገለች!

በትግራይ ክልል አበርገለ የጭላ ወረዳ በሚገኘው የጭላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከስምረት ጤና ጣቢያ የመጣች አንዲት እናት አምስት ህፃናትን በሰላም መገላገሏን የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያዎች አስታወቁ።

በወቅቱ እናቲቱን ያወለዱት አዋልድ ነርስ ገብረዮሐንስ ደስታ እንደገለጹት፡ እናቲቱ በማህፀኗ አምስት ህፃናትን የያዘች የነበረች ሲሆን፣ አራቱ ህፃናት ሙሉ እድገታቸውን ጨርሰው በጤና ተወልደዋል።

አምስተኛው ህፃን በሁለተኛው የእድገት ደረጃ (በአምስተኛው ወር አካባቢ) እድገቱ የቆመ ቢሆንም፣ እናቲቱ አራቱን ሙሉ ጤነኛ ህፃናት እና አንዱን እድገቱን ያላጠናቀቀውን ህፃን ጨምሮ በድምሩ አምስት ህፃናትን በሰላም ተገላግላለች።

ስለ እናቲቱ የተገለጹ አስደናቂ እውነታዎች፡እናቲቱ በቤተሰቧ የመንታ ዘር ያላት ከመሆኑም በላይ፣ እሷ ራሷ የመንታ ልጅ ነች! ይህ የመጀመሪያ ልጅ መውለዷ (በኩር) እንደሆነ ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት እናቲቱ ከባድ የኢኮኖሚ ችግር እንዳለባት የሆስፒታሉ ባለሙያዎች አክለው ገልጸዋል።

በአሁኑ ሰዓት የቅርብ ክትትል እየተደረገላቸው የሚገኙት እናትና ህፃናት በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተረጋግጧል።

(መረጃው፡- የአበርገለ የጭላ ወረዳ የመረጃና ህዝብ ግንኙነት ጽህፈት ቤት)

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቤተ-መንግስት ቢሮየክልሉን ህዝብ በሚወክል መልኩ ተገንብቶ አምሮና አሽብርቆ ለየት ባለ መልኩ ለህዝቡ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ ሆኗል።
07/09/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቤተ-መንግስት ቢሮ
የክልሉን ህዝብ በሚወክል መልኩ ተገንብቶ አምሮና አሽብርቆ ለየት ባለ መልኩ ለህዝቡ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ ሆኗል።

  - "የክልሉ ቤተ መንግስት መላው የክልላችንን ህዝብ ሊወክል እና ሊመጥን በሚችል መልኩ ተገንብቷል"  ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደበደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፤ የክልል ተቋማት ህንፃ ግንባታ ...
07/09/2026

- "የክልሉ ቤተ መንግስት መላው የክልላችንን ህዝብ ሊወክል እና ሊመጥን በሚችል መልኩ ተገንብቷል" ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፤ የክልል ተቋማት ህንፃ ግንባታ ፕሮጀክት አካል በፍጥነትና በጥራት ተገንብቶ ባማረ መልኩ በተጠናቀቀው የክልሉ ቤተ-መንግስት ለክልሉ አመራሮች የተዘጋጀ የጉብኝት እና የእራት መርሃ ግብር በቤተ-መንግስት ቅጥር ግቢ ተካሂዷል፡፡

በመርሃ ግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፥ የክልሉ ቤተ መንግስት ግንባታ መላው የክልሉን ህዝብ ሊወክል እና ሊመጥን በሚችል አግባብ ተግንብቶ በስኬት መጠናቀቁን ተናግረዋል።

አክለው ግንባታው እንግዳ ለመቀበል ፕሮቶኮሉን በጠበቅ እንዲሁም ባህላዊን ከዘመናዊ ዲዛይን ባጣመረ መልኩ ተግንብቶ መጠናቀቁ ገልፀዋል።

የክልሉ መንግስት የተቋማት የህንፃ ግንባታ ፕሮጀክት ባጠረ ጊዜ መጠናቀቅ ክልሉን በፅኑ መሠረት ላይ ከማኖር ባለፈ ካለው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አኳያ፤ በስድስቱም ክላስተር ማዕከላት የተጀመሩ ህንፃ ግንባታዎችን በጥራትና በፍጥነት አጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ግንባታው በዘጠኝ ወር መጠናቀቁ የፕሮጀክቶችን ጀምሮ በፍጥነት የማጠናቀቅ ባህል እያደገ መምጣቱን እንዲሁም ተጠናቆ ለዚህ እንዲበቃ የብዙዎች እጅ ያረፈበት መሆኑን የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ ለአንጆ ኑስ ኮንስትራክሽን፣ ለክልሉ ግንባታ እና ዲዛይን ቁጥጥር ባለስልጣን፣ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን እንዲሁም እገዛ ላደረጉ አካላት ሁሉ የላቀ ምስጋና አቅርበዋል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዱጼ ታምሩ የተመረቀው የቤተ መንግስት በመላው ሀገሪቱ እየተተገበሩ ካሉት ሜጋ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ እንደሆነ ገልፀዋል ።

የቤተ መንግስት ህንፃ በ2 ነጥብ 9 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ መሆኑን የገለፁት አቶ ዱፄ የመንግስት ስራዎችን በተቀናጀ መልኩ ለማከናወን የሚያግዝ እንደሆነም አብራርተዋል ።

በምረቃው መርሃግብሩ ርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ከበደ፣ የክልሉ ዋና አፈጉባኤ አቶ አለማየሁ ባዉዲ፣ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ፣የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጨላን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በመጨራሽም የቤተ መንግስቱን ምረቃ ምክንያት በማድረግ ለክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ ከወላይታ ዞን እና ከወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ባህላዊ የክብር ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

#ርዕሰመስተዳድርጽቤት
KMN -Kalacha Media Network

ባመረ መልኩ በተጠናቀቀው የክልሉ ቤተ-መንግስት የጉብኝት እና የእራት መረሃ ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛልበደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፤ የክልል ተቋማት ህንፃ ግንባታ ፕሮጀክት አካል በፍጥነትና በጥራ...
07/09/2026

ባመረ መልኩ በተጠናቀቀው የክልሉ ቤተ-መንግስት የጉብኝት እና የእራት መረሃ ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፤ የክልል ተቋማት ህንፃ ግንባታ ፕሮጀክት አካል በፍጥነትና በጥራት ተገንብቶ ባማረ መልኩ በተጠናቀቀው የክልሉ ቤተ-መንግስት ለክልሉ አመራሮች የተዘጋጀ የጉብኝት እና የእራት መርሃ ግብር በቤተ-መንግስት ቅጥር ግቢ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

የክልሉ መንግስት የተቋማት የህንፃ ግንባታ ፕሮጀክት ባጠረ ጊዜ መጠናቀቅ ክልሉን በፅኑ መሠረት ላይ ከማኖር ባለፈ ካለው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አኳያ፤ በስድስቱም ክላስተር ማዕከላት የተቋማት ህንፃ ግንባታዎችን በማስጀመር ግንባታቸው በጥራትና በፍጥነት ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ እንዲሆኑ በትኩረት በመስራት ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የተጀመሩ የህንፃ ግንባታዎች በፍጥነት መጠናቀቅ የክልሉን ተቋማት ተቋማዊ አቅም በማጠናከር፤ የተጀመረውን የማንሰራራት ስኬታማ ጉዞ በተሻለ አገልግሎት እንዲሁም የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ክልላዊና ሀገራዊ የዘላቂ ልማት ግቦችንና የሁለንተናዊ ብልጽግና ትልሞችን ከግብ በማድረስ የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሚናቸው ከፍተኛ ነው፡፡

የዚሁ አካል በወላይታ ሶዶ ማዕከል በግንባታ ላይ ከነበሩ የተቋማት የህንፃ ግንባታ ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነው የክልሉ ቤተ-መንግስት ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ተገንብቶ በስኬት የተጠናቀቀ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት የክልሉ መንግስት የ2018 ዓ.ም የከፍተኛ አመራሮች የማጠቃለያ መድረክ መጠናቀቁን ተከትሎ የጉብኝትና የእራት መርሃ ግብር መዘጋጀቱ ታውቋል፡፡

መርሃ ግብሩ በኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች የጸሎትና ምርቃት በይፋ የሚጀመር ሲሆን፤ ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩም በመርሃ ግብሩ መልዕክት ያስተላልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም የጉብኝትና የእራት ግብዣን ጨምሮ ስለ ቤተ-መንግስት ህንፃ ፕሮጀክቱ እና ስለግንባታው ሂደት ማብራሪያ በማቅረብ ሌሎች በግንባታ ላይ ያሉ የክልል ተቋማት ህንፃ ግንባታዎችን በፍጥነትና በጥራት ገንብቶ ለማጠናቀቅ ተሞክሮ ይወሰድበታል ተብሎም ይጠበቃል፡፡

በመርሃ ግብሩ ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ የክልሉ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ገ/መስቀል ጫላ፤ የክልሉ አስተባባሪ አካላት፤ አፈ ጉባዓዎች፤ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፤ የዞንና የፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ከፍተኛ አመራሮች፤ የረ/ፖ/ከተማ ከንቲቦችን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ አመራሮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡

በ2018 በጀት ዓመት ከፍተኛ የስራ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ተቋማት ፣ ዞኖች እና የሪጂዮ ፖሊስ ከናተሞች  እውቅናና ሽልማት ተሰጣቸውበክልሉ በዚሁ በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት በኢኒሼቲቮች...
07/09/2026

በ2018 በጀት ዓመት ከፍተኛ የስራ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ተቋማት ፣ ዞኖች እና የሪጂዮ ፖሊስ ከናተሞች እውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው

በክልሉ በዚሁ በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት በኢኒሼቲቮች ተሻለ የተግባር አፈጻጸም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ መዋቅሮች እና የክልል አስፈጻሚ ተቋማት መድረኩ ዕውቅና ተሰጥቷል።

* የክልሉ ገቢዎች ቢሮ እና የወላይታ ፣ ጋሞ እና ጌዴኦ ዞኖች በላቀ አፈፃፀም የሚኪና ተሸላሚ ሆነዋል።

* ከክልል ቢሮዎች ከፍተኛ አፈፃፀም የስመዘገቡ
የክልሉ ፍትህ ቢሮ፣ ፋይናንስ ቢሮ፣ ፕላን ቢሮ ፣ ገቢዎች ቢሮ፣ ጤና ቢሮ፣ መስኖና ቆላማ ቢሮ፣ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ፣

* ከዞን መዋቅሮች:- ኢኒሼቲቮችን በመፈፀም የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገብ የመኪና እና ልዩ ልዩ ሽልማቶችን የተሸልመዋል ፡- 1ኛ ወላይታ ዞን 2ኛ ጋሞ ዞን 3ኛ ጌዴኦ ዞን፣ ተሸላሚ ሆነዋል።

*ከሪጂዮ ፖሊስ ከተሞች ፡- ኢኒሼቲቮችን በመፈፀም የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገቡ የሪጂዮ ፖሊስ ከተሞች 1ኛ- አርባምንጭ ከተማ 2ኛ- ወላይታ ሶዶ ከተማ 3ኛ ዲላ ከተማ አስተዳደር ተሻላሚ ሆነዋል ።

* እንዲሁም ኢኒሼቲቮችን በመፈፀም የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ጎፋ ፣ አሪ ፣ ደቡብ ኦሞ ፣ ኮንሶ፣ ባስኬቶ እና ጋርዱላ ዞን አስተዳደር ተሸላሚ ሆኖዋል።

በመድረኩ ኢኒሼቲቮችን በመፈፀም ጅምር አፈፃፀም ላስመዘገቡ አሌ ፣ ኮሬ እና ቡርጂ ዞን ተሸልመዋል።

የእውቅናው መስፈርት በግብርና ልማት ፣ ከተማና መሰረተ ልማት ፣ ትምህርት ልማት ፣ ጤና ልማት፣ ቱሪዝም ልማት፣ ንግድ ኢንደስትሪ ልማት ፣ ገቢ ንቅናቄ፣ ስራና ክህሎት እንዲሁም የዲጂታላይዘሽን ዘርፎች ላይ ያተኮሩ ኢኒሼቲቮችን ትኩረት ያደረገ መሆኑን የርዕሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪ ቦሻ ቦንቤ ( ዶ/ር ) የምዘና መስፈርቱን ባብራሩበት ወቅት ገልፀዋል።

መድረኩ ተቋማት ከክቡር ርዕሰ መስነዳድሩ ጋር የግብ ስምምነት በመፈራረምም ተጠናቋል።

  - ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት ክልላዊ የከፍተኛ አመራሮች መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛልርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት ክልል አቀፍ የከፍተኛ አመራሮች መድረክ በወ...
07/09/2026

- ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት ክልላዊ የከፍተኛ አመራሮች መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት ክልል አቀፍ የከፍተኛ አመራሮች መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ በመካሄድ ላይ ሲሆን፤ መድረኩ በዋናነት በክልሉ መንግስት የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ አፈጻጸም፤ በ2019 መሪ ዕቅድ እንዲሁም የቀጣይ 5 ዓመት ጠቋሚ ስትራቴጂክ ዕቅድ ዙሪያ የሚመክር ይሆናል፡፡

የ2018 ዓ.ም ማጠቃለያ የሆነው ይሄው የአመራሮች መድረክ፤ የክልሉ መንግስት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለክልላዊ እና ሀገራዊ የሰላም፤ የልማትና የብልጽግና ራዕይ ስኬት ባከናወናቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት የተመዘገቡ ውጤቶችን በመገምገም፤ ለ2019 የላቀ አፈጻጸም ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

መድረኩ የዞን፤ የረጂዮ ፖሊስ ከተሞች እና የክልል አስፈጻሚ ተቋማት የበጀት ዓመቱን አጠቃላይ የተግባራት አፈጻጸም መሠረት ያደረገ የምዘና ውጤት ዙሪያም የሚወያይ ሲሆን፤ ይህም በክልሉ በየደረጃው ያሉ መዋቅሮችና አስፈጻሚ ተቋማት የማስፈጸም አቅም በማጎልበት ለተሻለ ውጤት ለማብቃት የጎላ ፋይዳ የሚኖረው ይሆናል፡፡

በተጨማሪም መድረኩ የክልሉን የብልጽግና ፍኖቴ ካርታ፤ ሀገራዊ የዘላቂ ልማት ግቦችንና የሁለንተናዊ ብልጽግና ራዕይ ማዕከል አድርጎ በተዘጋጀ የክልሉ መንግስት የቀጣይ 5 ዓመት ጠቋሚ ስትራቴጂክ ዕቅድ ዙሪያም የሚመክር ከመሆኑም በላይ የክልሉ አስፈጻሚ ተቋማት የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ የግብ ስምምነት የሚፈራረሙ ይሆናል፡፡

በመድረኩ የተገኙት ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በተለይ የክልሉ መንግስት የትኩረት አቅጣጫ በሆኑ ቁልፍ የልማት ዘርፎችና ሀገራዊ የልማት ኢኒሼቲቮች የውጤት ዘላቂነትን ከማረጋገጥ ባሻገር በላቀ አፈጻጸም የክልሉን ሕዝብ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ ቀጣይ አቅጣጫዎች በማስቀመጥ ለአመራሩ ስምሪት የሚሰጡ ይሆናል፡፡

በዚህም መድረኩ የአመራሩን የዓላማ፤ የአመለካከትና የተግባር አንድነት በማጠናከር ለቀጣይ የዘላቂ ሰላምና ልማት ተልዕኮ ያዘጋጃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የክልሉ መንግስት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በክልሉ ህዝብ ግንባር ቀደም ተሳትፎ በሁሉም የልማት አውታሮች ዘርፍ ብዙ ውጤታማ የሰላም፤ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በመስራት አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉ ይታወቃል፡፡

በክልሉ በዚሁ በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት፤ በተሻለ የተግባር አፈጻጸም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ መዋቅሮች እና የክልል አስፈጻሚ ተቋማት መድረኩ ዕውቅና ይሰጣል ተብሎም ይጠበቃል፡፡

በመድረኩ ከክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ በተጨማሪ የክልሉ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ገ/መስቀል ጫላ፤ የክልሉ አስተባባሪ አካላት፤ አፈ ጉባዓዎች፤ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፤ የዞንና የፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ከፍተኛ አመራሮች፤ የረ/ፖ/ከተማ ከንቲቦችን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ አመራሮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡

#ርዕሰመስተዳድርጽቤት
KMN -Kalacha Media Network

ከተሞችን በማዘመን የብልጽግና ማዕከላት ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል :- አቶ ብርሃኑ ዘውዴ  ጳጉሜ 2/2018 ዓ.ም በጋሞ ዞን ሰላምበር ከተማ የተሟላ ዘመናዊ የማዘጋጃ ቤት አገልግሎ...
07/09/2026

ከተሞችን በማዘመን የብልጽግና ማዕከላት ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል :- አቶ ብርሃኑ ዘውዴ

ጳጉሜ 2/2018 ዓ.ም በጋሞ ዞን ሰላምበር ከተማ የተሟላ ዘመናዊ የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት በይፋ ተጀምሯል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ባስተላለፉት መልዕክት ክልሉ ከተሞችን በማዘመን የብልጽግና ማዕከላት ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

መንግሥት ለከተሞች በሰጠው ትኩረት ፈጣን የልማት እድገት መመዝገቡን የጠቆሙት ሀላፊው ለውጥ በዘላቂነት ለማስቀጠል በሁሉም ከተሞች ዘመናዊ የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት በማስፋፋት ነዋሪዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

የማዘጋጃ ቤቶች የመሬትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የሚነሱባቸው ተቋማት ሆነው መቆየታቸውን ያስታወሱት የቢሮው ኃላፊ፣ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት በ29 ከተሞች የማዘመን ሥራዎች በትኩረት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።

በክልሉ የከተሞች ማዘመን ሥራዎች በመከናወናቸው የተገልጋይ እርካታ ከ40 በመቶ ወደ ከ70 በመቶ በላይ ማድረስ መቻሉንም አቶ ብርሃኑ ተናግረዋል።

ህብረተሰቡን የልማቱ ባለቤት በማድረግና በማሳተፍ የተጀመሩትን አበረታች የልማት ሥራዎች ማስቀጠል ከተቻለ ሰላምበር ከተማ በአጭር ጊዜ የፈርጅ ለውጥ ልታደርግ እንደምትችል ጠቁመዋል።

የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ደምሴ አድማሱ በበኩላቸው፣ ዘመናዊው የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት ለህብረተሰቡ ከወረቀት ንክኪ ነፃ፣ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የባለጉዳዮችን እንግልት የሚቀንስ መሆኑን ገልጸዋል።

ከሰላምበር ወደ ዲታና አርባ ምንጭ በቅርቡ የትራንስፖርት አገልግሎት መጀመሩን የጠቆሙት ዋና አስተዳዳሪው፣ ከተማዋ በእድገትና በመነቃቃት ላይ በመሆኗ አልሚ ባለሀብቶች በመምጣት ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

በቀጣይም የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ ከመገፋፋት ይልቅ አንድነትንና ወንድማማችነትን በማጠናከር፣ በቅንጅትና በመተባበር በጋራ መስራት እንደሚገባ ዶ/ር ደምሴ አሳስበዋል።

አያይዘውም ዋና አስተዳዳሪው፣ ዘመናዊ የማዘጋጃ ቤት አገልግሎቱ ወደ ሥራ እንዲገባ አስተዋጽኦ ላበረከቱ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ምስጋና አቅርበዋል።

የጋሞ ዞን ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አብርሃም አርጋው፣ ከተሞችን በማዘመን ለነዋሪዎች ምቹና ተስማሚ ለማድረግ በአረንጓዴ ልማት፣ በመሠረተ ልማትና በሌሎች የልማት ዘርፎች በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዞኑ ሰባት የከተማ አስተዳደሮች እንዳሉ የገለጹት አቶ አብርሃም፣ ከእነዚህ ውስጥ ሦስቱ ዘመናዊ የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት ማስጀመራቸውንና ቀሪዎቹንም በአጭር ጊዜ ለማስጀመር እየተሰራ መሆኑን አሳውቀዋል።

የሰላምበር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዳርዛ ደምሴ በበኩላቸው፣ ከተማዋ የከተማ አስተዳደር መዋቅር ካገኘች ከስምንት ዓመታት ወዲህ በርካታ የልማት ሥራዎችን በማከናወን ለነዋሪዎቿ ምቹና ተስማሚ ከተማ ለማድረግ ጥረት ሲደረግ መቆየቱን ገልጸዋል።

በመርሃ ግብሩ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር አመራሮች ተገኝተዋል።

ከ“ዶሮ ሽጠን ዶዘር እንገዛለን” መፈክር ወደ ተግባር፤ ንቅናቄ ድጋፍ ላበረከቱ አመራሮች እውቅና ተሰጠ::  - ጳጉሜን 1/2018 ዓ.ም በጎፋ ዞን የመሎ ሕዝቦች “ዶሮ ሽጠን ዶዘር እንገዛለን...
06/09/2026

ከ“ዶሮ ሽጠን ዶዘር እንገዛለን” መፈክር ወደ ተግባር፤ ንቅናቄ ድጋፍ ላበረከቱ አመራሮች እውቅና ተሰጠ::

- ጳጉሜን 1/2018 ዓ.ም በጎፋ ዞን የመሎ ሕዝቦች “ዶሮ ሽጠን ዶዘር እንገዛለን” በሚል ታላቅ መፈክር የጀመሩት የመንገድ መሠረተ ልማት ጥያቄን በራስ አቅም የመፍታት ንቅናቄ ውጤት በማስመዝገቡ፣ ለስኬቱ የላቀ ድርሻ ላበረከቱ የክልልና የጎፋ ዞን ከፍተኛ የመንግስትና የፓርቲ አመራሮች ልዩ እውቅናና የፍቅር ስጦታ ተበርክቷል።

በመሎ ኮዛ ወረዳ ላሃ ከተማ የተገዙትን የመንገድ ሥራ ማሽነሪዎች ለማስመረቅ በተዘጋጀው መርሐ ግብር፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ጥላሁን ከበደን ጨምሮ የክልል፣ የጎፋ ዞንና ከአጎራባች መዋቅሮች የተገኙ ከፍተኛ የመንግስትና የፓርቲ አመራሮች ተገኝተዋል።

የመሎ ሕዝቦች በጠንካራ የማህበረሰብ ተሳትፎ የጀመሩት ይህ ንቅናቄ፣ የሕዝቡን የቆየ የመንገድ ጥያቄ በጋራ አቅም ለመፍታት ያለውን ቁርጠኝነት ወደ ተግባር የቀየረ ተሞክሮ ሆኗል።

በንቅናቄው የተገዙት የመንገድ ሥራ ማሽነሪዎችም የአካባቢውን የመሠረተ ልማት ችግር በራስ አቅም ለመፍታት ጠቃሚ አቅም ፈጥረዋል።

ለዚህ ስኬት በሐሳብ፣ በማበረታታትና በተለያዩ ድጋፎች አስተዋፅኦ ላበረከቱ አመራሮች በመርሐ ግብሩ ወቅት የእውቅና ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል።

በተለይም ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ፣ በኢፌድሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ዶ/ር ተስፋዬ በልጅጌ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የወላይታ ሶዶ ክላስተር አስተባባሪ እና ለጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ ልዩ እውቅና ተሰጥቷል።

በተጨማሪም ለንቅናቄው ውጤታማነት በተለያዩ መንገዶች ድጋፍ ላበረከቱ ሌሎች የክልሉና የጎፋ ዞን ከፍተኛ አመራሮች የእውቅናና የፍቅር ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

የእውቅናና የፍቅር ስጦታዎቹን የመሎ ኮዛ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙሉነህ አውሳቶ እና የላሃ ከተማ ከንቲባ ክቡር አሸናፊ ጮራ ለተሸላሚ አመራሮች አበርክተዋል።

“ዶሮ ሽጠን ዶዘር እንገዛለን” የሚለው የመሎ ሕዝቦች መፈክር፣ ሕዝብ በጋራ ዓላማ ተደራጅቶ የራሱን የልማት ጥያቄ ለመፍታት ሲነሳ ትልቅ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚቻል በተግባር ያሳየ ሆኗል።

ይህ የመሎ ሕዝቦች ተሞክሮ ሕዝብ፣ አመራሩና መንግስት በጋራ ሲቆሙ የቆዩ የመሠረተ ልማት ጥያቄዎችን በራስ አቅም ወደ ተጨባጭ መፍትሔ መቀየር እንደሚቻል ያሳየ አርዓያ ተሞክሮ መሆኑ ተገልጿል።

via :- Gofa Zone Government Communication Affairs Department KMN -Kalacha Media Network

  - የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለ8 መቶ 40 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መጪውን ...
06/09/2026

- የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለ8 መቶ 40 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መጪውን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ የይቅርታ አዋጁን መስፈርት ላሟሉ 8 መቶ 40 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ይቅርታ የተደረገላቸው የሕግ ታራሚዎች በማረሚያ ቤት ቆይታቸው መልካም ሥነ-ምግባር ያሳዩና በሕግ በተደነገገው አግባብ የይቅርታ መስፈርትን ማሟላታቸው በክልሉ መንግስት የይቅርታ ቦርድ ተጣርቶ የቀረቡ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የሕግ ታራሚዎቹ በመደበኛ የይቅርታ ሕግ እና ሌሎች ተጨማሪ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተብለዉ በልዩ ሁኔታ የቀረቡ፤ በማረሚያ ቆይታቸው ስለመታረማቸውና ስለመታነፃቸው ማረጋገጫ የቀረበላቸው መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በዚሁ መሰረት የይቅርታው ተጠቃሚዎች በይቅርታ አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት አዋጅ እና አዋጁን ለማስፈፀም በወጣው ደንብ ይቅርታ በማያስከለክሉ ወንጀሎች ተሳትፈው፡-

በማረሚያ ቤት የቆዩ፤ በጤና ችግር፤ በዕድሜ መግፋትና ከሕጻናት ጋር አብረዉ የታሰሩ እንዲሁም ከተፈረደባቸው ሲሶ (1/3) እና ከግማሽ (1/2) በላይ የፍርድ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ መሆናቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ አስረድተዋል።

የይቅርታ ተጠቃሚ ከሆኑት የሕግ ታራሚዎች መካከል 56ቱ ሴቶች ሲሆኑ፤ 7 መቶ 84 ደግሞ ወንዶች መሆናቸውን አመልክተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ የይቅርታው ተጠቃሚ የሆኑ የሕግ ታራሚዎች የይቅርታን እሴት ተላብሰው ሰላም ወዳድ፣ ለሕግ ተገዥና አምራች ዜጋ በመሆን የበደሉትን ህብረተሰብ በማገልግል በልማት ሊክሱ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ህብረተሰቡም ይቅርታ የተደረገላቸው የህግ ታራሚዎች በፈፀሙት ጥፋት የተፀፀቱና በአግባቡ ታርመው የወጡ መሆኑን በመረዳት መልካምና አምራች ዜጋ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

South Ethiopia Regional government Communication Affairs Bureau
KMN -Kalacha Media Network

ወደ ሰፖርቱ ስንመለስ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ተጠባቂዉ ጨዋታ  #አርሴናል vs  #ቼልሲ ያደርጋሉ ማን ያሸንፍ ይሁን?
06/09/2026

ወደ ሰፖርቱ ስንመለስ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ተጠባቂዉ ጨዋታ
#አርሴናል vs #ቼልሲ
ያደርጋሉ ማን ያሸንፍ ይሁን?

Address

Arba Minch'

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when KMN -Kalacha Media Network posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category