Qafarey Baritaay Iggimak Nawqay Page

Qafarey Baritaay Iggimak Nawqay Page Qafar ayyunta Qulul kee Baacay Iggimak Tawquk Xiqqa Haamal Bar Kee Laqo Macleyo!!

14/02/2019
የታሪክ ባለቤት (ሀቢብ መሀመድ ሀሰን የታሪክ ተመራማሪ)written by:- (Qafarey Baritaay Iggimak Nawqay) የአፋር ታሪክ.========ጥንታዊ የአፋር ታሪክየአፋር የሚለ...
14/11/2018

የታሪክ ባለቤት (ሀቢብ መሀመድ ሀሰን የታሪክ ተመራማሪ)
written by:- (Qafarey Baritaay Iggimak Nawqay) የአፋር ታሪክ.
========
ጥንታዊ የአፋር ታሪክ
የአፋር የሚለው ስያሜ አመጣጥ
የአፋር ህዝብ በሌሎች ማህበረሰቦች ዘንድ የተለያዩ ስያሜዎች የተሠጠቸው ሲሆን ይህም በአረቦች ደንከል፤ በአማሮች አዳል፣በኦሮሞ እና ሶማሊ ኦዳሊ የሚል ስያሜ የተሰጠቸው ሲሆን አረቦች ደንከል የሚል ስያሜ ለአፋር የሰጡት በጥንት ግዜ በቀይ ባህር አካባቢ ከአረቦች ጋር ከፍተኛ የሆኔ የንግድ ልውውጥ ሲያደርጉ በነበሩ እና የአካባቢው ገዥ መደብ የነበሩ ጥንታዊ አፋር ጎሳዎች ማለትም ደንከሊ ከሚባል የአፋር ጎሳ ስያሜ መነሻ በማድረግ ነበር፡፡ይህም ያሲን መሀመድ የተባለው ጸሃፊ political history of Afar in Ethiopia and Eretria በሚለው ጹሁፋቸው በገጽ-41 ላይ እዲህ በማለት አስቀምጡዋል(Similarly, due to historic commercial contact between Arabian sailors and the Dankali clan located around Baylul, who ruled the kingdom of Dankali(15th-17thc),Arabs gave the name Danakil to all the Afar across the Red sea coast.) በሌሎች የኢትዮጵያ ብህረሰቦች ዘንድ ለአፋር አዳል የሚለውን ስያሜ የሰጡት ከ16ኛው
ክ/ዘመን መላው ምስራቅ አፍሪካ ማለትም ኢትዮጵያ፣ኤርትራ፣ጅቡቲና ሶማሊያ ጨምሮ ሲገዛ የነበረው የአዳል መንግስት አጠቃላይ የጦር ሀይሉና ገዥው መደብ አፋሮች ስለነበረ ነው፡፡ ይህም ENCYCLOPAEDIA ATHIOPICA VOLUME -1 A-C ገጽ 71 ላይ እንዲህ ገልጾታል(since the name Adal seems etymologically to have some connection with the dankali tribe Ada-ali mentioned in the chronicle of awsa and with the Somali name their odali for their Dankali neighbours,the main population of Adal(Adal sultanate) may have been of Afar stock.)
ሌላው ዶ/ር አብደላ አብዱ አዱ “Afar a nation on trial” በሚለው መጽሃፋቸው ሌሎች ህዝቦች ለአፋር የተለያዮ ስያሜ ለምን እና እንዴት እንዴት ሰጡ ሲያብራራ” however they are known by different names among the neighboring people. They are known as “Danakil” among arabs, “Adal” among the amharas, “Adali” among oromos, “odaali” among the Somalis, “Teltal” among the tigreans. The origin of these names is difficult to trace but certain suggestions could be made as to where and how these name emerged. The “Danakil” has been used by northern afar neighbors and across the red sea by the arabs,it may have derived from the ancient afar state of Dankali. In the south and west afar are known as “Adal”. Adal was also an ancient afar state which dominated the southern and western portion of the region. Another alternative origin to the names are suggested the clan: both Dankali and Adali are clans of the afars to be found in then north and southern parts of the region respectively.” ይህም በአጭሩ በአማረኛ ሲገልጸው አረቦች እና ሰሜናዊው ጎረቤቶቹ አፋርን ደንከል ብሎ የጠሩት በቀይ ባህር አካባቢ ገዥ የነበረው ጥንታዊው የደንከል ስርዎ-መንግሰት ስያሜ ተንተርሶ ሲሆን፤ በደቡብ እና በምእራብ ያሉ ጎረቤቶቻቸው አፋርን አዳል ብሎ የጠሩት ከአዳል(አፋር) ሰርዎ-መንግስት ስያሜ በመነሳት ሲሆን ሌለው ደሞ ደንከል እና አዳሊ(አድ-አሊ) ሁለቱም በሰሜን እና በደቡብ የሚገኙ ጥንታዊው የአፋር ጎሳዎች ስያሜ ተንተርሶ ሊሆን ይችላል ብሎዋል፡፡
ይሁንና የአፋር ህዝብ የዘር ግንዱ ከኩሽ ነገድ ሲሆን ብዙ የታሪክ ተመራማሪወች አፋር የሚል ስም ያገኙት አል-መአፋራ ከሚባሉ በየመን ከሚገኙ ጥንታዊ ጎሳዎች ነው ይላሉ፡፡ ይህም ዶ/ር ሃሽም አልማንሃል በሚለው መጽሃፋቸው በገጽ-34 ላይ እንዲህ ይላል(በአፋር ዙሪያ የሚኖሩ ልዩ ልዩ ብህረሰቦችን አፋሮችን በተለያዩ ስም ሲጠሯት ይሰማሉ፡፡ ይሁን እንጅ ትክክለኛ ስሟ አፋር ሲሆን የቃሉም አጠራር “አል-መአፋራ” ከሚለው ከየመን ከመጡ የሀመዳን ጎሳዎች የተወረሰ ሳይሆን አይቀርም፡፡
ዶ/ር ሃሽም,አልማንሃል,ገጽ-34,2000 ዓ.ም) በማለት አፋር የሚለው ቃል ከየመን ከሚኖሩ አልመአፋራ ጎሳ የተወሰደ መሆኑን ግምቱን አስቀምጡዋል ፡፡ አንደንድ ታሪክ ተመራማሪወች ለምሳሌ ራይሞንዶ ፍራንቺቲ(Rainmondo Franchetti) አፋር የሚለው ቃል የመጠው በመጽሃፍ ቅዱስ በተጠቀሰው ኦፊር(ophir) የሚባልና በጥንት ግዜ በወርቅ የተከበረ ቦታ ሲሆን ይህም በአፋር ብዙ የወርቅ ክምችት ስላሌ አፋር ስያሜውን ያገኙት ከዚሁ ሳይሆን አይቀሪም በማለት ግምታቸውን አስቀምጡዋል፡፡ ሌላው አሃው አሊ የተባለው የታሪክ ጸሃፍ ኤርትራ እስከየት ድረስ ቢሚለው መጽሃፋቸው ፍርናንዶ ፋራንኪቲን በመጥቀስ አፋር የሚለው ቃል የመጠው ኦፊር/ophir/ ከተባለውና በወርቅ ክምችት ከሚገኝበት ደንካሊያ አካባቢ ነው በማለት የገለጸ ሲሆን በተጫማሪም ንግስት ሳባ ለንጉስ ሰለሞን በስጦታ የወሰደችውን ወርቅ ያወጡት ከዚሁ ደንካሊያ አከባቢ ነበር በማለት ግምቱን አስቀምጡዋል፡፡ይህም በመጽሃፋቸው በገጽ-6 እንዲህ በማለት አስቀምጡዋል (kusaq abe fairnando farankiti Qafar inta qangara”ophir” inta qanagarak temeete wo migaq duma dankaaliyah rakaakayak dahab akak ayyaaquk yenen aracah abak yenen. Mmalikat saba nabilla seleemanah acawah beyte dahab akak ayyaaquk yeneenim woo araca iyya,woo saaku dankaaliya malikat saabah xintoh gubat tenem aydaadi yascasse.) አንደንድ ታሪክ ተመራማዎች ደሞ አፋር ህዝብ በኦማን አልሞዳይቢ እና ዱሩ ድንበር በስተደቡብ እና ከዋሂባ ከሚባል አሻዋማ አካባቢ ምእራብ በኩል ከሚኖሩ አፋር/ኢፋር ከሚባሉ ጎሳ ጋር የዘር ግንድ ይኖራቹዋል ተብሎ ይገመታል ፡፡ ይህም ENCYCLOPAEDIA ATHIOPICA VOLUME -1 A-C ገጽ 116 ላይ እንዲህ ገልጾታል(due to continues Arabian influx a possible link with the oman group called afar or ifar,living south of al-mudaibi and of the duru territory, west of the wahiba sands. The same eponymous ancestor afar is mentioned in the genealogies( women in the ifar’s case).
ሌላው ዲዴየር ሞሪን(Didier Morin) የተባለው ጸሃፊ አፋር የሚለው ስም የመጠው ከኦማን አፋር ወይም ኢፋር ከተባለው ጎሳ ሳይሆን አይቀሪም በማለት ግምቱን አስቀምጦ ግን የዚህ ኦማን ህዝብ እና የአፋር ህዝብ ያላቸውን ግንኙነት ምንም ያልተባለበትና የተረሳ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሱዋል፡፡ ይህም ዲዴየር ሞሪን(Didier Morin) በጹሁፋቸው እንዲህ በማለት ጽፉዋል(the name afar as having a possible but forgotten link with the omani group called afar ifar).
በአሁኑ ሰአት የኦማን ሴቶች እደ-ጥበብ ውጤቶችና አሰራራቸው ከአፋር ሴቶች እደጥበብ ምርቶችና አሰራራቸው ጋር እጅግ ተመሰሳሳይነት አለው፡፡ ይህም ሁለቱ ማህበረሰቦች የዘር ግንድ ሊኖራቸው ይችላሉ የሚለውን መላምት ያጠናክራል ማለት
ይቀጥላል-----
Ni Aydaadu Dudda Luk Naaxigeemi
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

14/11/2018

"ደስታ እና ጥሩ ነገር ከመልካምነት ይገኛል"

11/10/2018
"Ni-Milaagi Ni Gabat Yan  Ni-Ummattey"
30/09/2018

"Ni-Milaagi Ni Gabat Yan Ni-Ummattey"

የሀገራችን ሠላም ሁሉም እንተባበር!!
23/09/2018

የሀገራችን ሠላም ሁሉም እንተባበር!!

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Qafarey Baritaay Iggimak Nawqay Page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share